Free Clothing and showering

መና የአረጋውያንና የአዕምሮ ህሙማን መርጃ ማዕከል ለማህበረሰቡ ከሚያገለግባቸው ስራዎች መካከል አንዱ የሆነው የጎዳና ሻወር አገልግሎት ነው። ይሄ የጎዳና ሻወር ታሳቢ ተደርጎ የተጀመረው ጎዳና ላይ ለሚውሉና ለሚያድሩት ለጎዳና ተዳዳሪ ልጆች ቢሆንም ግን ሌሎችንም ሰዎችንም ያካትተ ግልጋሎት ነው።

የሻወር አገልግሎቱ የሚከናወንበት በሳምንት አንድ ቀን ዕለተ ቅዳሜ ከጠዋቱ 2:00 ሰዓት ጀምሮ በጎንደር ከተማ የምስራች አካባቢ በተለምዶ በጅሮንድ ደረጃ ስር ላይ በማዕከሉ በጎ ፈቃደኞች ይሠጣል።

 

በዚህ ፕሮግራም ስር ከሚደረጉ ግልጋሎቶች ወይንም ከሚሰሩ ስራዎች ዝርዝር:- 

1ኛ- የጎዳና ልጆች ካሉበት መጥፎ ሁኔታ መመለስ ማለትም እንደ ሱስ ካለባቸው ከሱስ ማላቀቅ ፣ የስራ ዕድሎችን ማመቻቸት ።

2ኛ- ሰው የለኝም የሚሉትንና የእውነት ሰው የሚናፍቁትን የጎዳና ልጆች ሰው እንዳላቸው ማሳየት ፣ ከነሱ ጋር ጊዜን ማሳለፍ ፣ ማጫወት ፣ እነሱን መረዳት ፣ መንከባከብ እና መምከር ።

3ኛ- ገላቸውን ማጠብ

4ኛ- የወንዶችን ፀጉር ማስተካከልና የሴቶችን ፀጉር መስራት።

5ኛ- ጥፍራቸውን መቁረጥ።

6ኛ- የቅዳሜ ቁርሳቸውን መሸፈን። እነዚህንና ሌሎችንም ግልጋሎቶችን በመና የአረጋውያንና የአዕምሮ ህሙማን መርጃ ማዕከል በጎ ፈቃደኞች እንሰጣለን። 

ለጎዳና ሻወሩ ፕሮግራሙ የሚሆኑና የሚያስፈልጉን ነገሮች :- የንፅህና መጠበቂያዎችን እንደ ሳሙና ፣ ቅባት ፣ የሴቶች ንፅህና መጠበቂያ (ሞዴስ) ፣ የገላ ማሻዎችን እንዲሁም ያገለገሉ አልባሳቶችን ጫማዎችን ፣ ፅሀፍቶችን እናንተም በአካል በመገኘት ወይንም እኛም ካለችሁበት ድረስ በመምጣት እና በማይት በድጋፍ መልኩ በመለገስ የታላላቆቻችን ምርቃን እንድትወሰዱ ፣   በተጨማሪም የማዕከሉ አንድ አባልና በጎ ፈቃደኛ እንድትሆኑና የአንድ ሰው ፈገግታ ምክንያት እንድትሆኑልን ስንል እንጠይቃለን ። 

Scroll to Top